bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 83
Psalms 83
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ! እባክህ ዝም አትበል፤ አትተወን፤ ችላ አትበል!
2
እነሆ፥ ጠላቶችህ ዐምፀዋል፤ የሚጠሉህ ሁሉ ራሳቸውን በአንተ ላይ አንሥተዋል።
3
በሕዝብህ ላይ በስውር ያደባሉ፤ አንተ በምትጠብቃቸው ላይ ያሤራሉ።
4
“እስራኤል ለዘለዓለም የተረሳ እንዲሆን ኑ፤ መንግሥታቸውን እንደምስስ” ይላሉ።
5
በአንድነት በአንተ ላይ አሤሩ፤ በአንተ ላይ ለመነሣት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረጉ።
6
እነርሱም የኤዶም፥ የእስማኤል፥ የሞአብ፥ የአጋርያን፥
7
የጌባል፥ የዐሞን፥ የዐማሌቅ፥ የፍልስጥኤምና የጢሮስ ሰዎች ናቸው።
8
አሦርም የሎጥን ልጆች በመርዳት ከእነርሱ ጋር ተባብራለች።
9
በምድያማውያን፥ በሲሣራና በያቢንም ላይ በቂሾን ወንዝ ያደረግኸውን በእነዚህም ላይ አድርግ።
10
እነርሱን በዔንዶር ድል አደረግሃቸው፤ ሬሳቸውም በሜዳ ላይ በስብሶ ቀረ።
11
በዖሬብና በዜብ ላይ ያደረግኸውን በእነርሱም መሪዎች ላይ አድርግ፤ በዜባሕና በጻልሙናዕ ያደረግኸውን በእነርሱም ገዢዎች ላይ አድርግ።
12
እነርሱ “የእግዚአብሔርን ሕዝብ ርስት የራሳችን እናደርጋለን” ብለው ነበር።
13
ስለዚህ አምላኬ ሆይ! እንደ ትቢያ፥ በነፋስም እንደሚወሰድ ገለባ በትናቸው።
14
እሳት ደንን እንደሚያጋይ፥ የእሳት ነበልባልም ተራራዎችን እንደሚያቃጥል
15
በሞገድህ አባራቸው፤ በዐውሎ ነፋስህም አስደንግጣቸው።
16
እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ይሹ ዘንድ ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን፤
17
ዐፍረው ለዘለዓለም ተስፋ እንዲቈርጡ አድርግ፤ ተዋርደውም እንዲጠፉ አድርግ።
18
በምድር ሁሉ ላይ ጌታና ሁሉን ቻይ አምላክ አንተ እግዚአብሔር እንደ ሆንክ ይወቁ።
← Chapter 82
Chapter 84 →