bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 82
Psalms 82
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር በሰማያዊው ጉባኤ አማልክት ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ በመካከላቸው ተገኝቶ ፍርድ ይሰጣል፦
2
“እስከ መቼ ትክክል ያልሆነ ፍርድ ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼ ለክፉዎች ታዳላላችሁ?
3
ለደካሞችና ለሙት ልጆች በትክክል ፍረዱ፤ የድኾችንና የተጨቈኑትን ሰዎች መብት ጠብቁ።
4
ደካሞችንና ችግረኞችን አድኑ፤ ከክፉዎችም ጥቃት አስጥሉአቸው።
5
“እነርሱ ግን ምንም አያውቁም፤ አይገባቸውምም፤ በጨለማ ይመላለሳሉ፤ በዚህም ጊዜ የምድር መሠረትዋ እየተናወጠ ነው።
6
‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል እግዚአብሔር ልጆች ናችሁ’ አልኩ።
7
ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፤ የሕይወታችሁም ፍጻሜ እንደ ማንኛውም ምድራዊ ገዢ ነው።”
8
አምላክ ሆይ! ተነሥ! መንግሥታት ሁሉ ያንተ ስለ ሆኑ ለዓለም ፍርድን ስጥ።
← Chapter 81
Chapter 83 →