bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 84
Psalms 84
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
የሠራዊት አምላክ ሆይ! ቤተ መቅደስህ ምንኛ ተወዳጅ ነው!
2
የቤተ መቅደስህን አደባባይ በጣም እናፍቃለሁ፤ ለሕያው አምላክ በሙሉ ልቤ በደስታ እዘምራለሁ።
3
ንጉሤና አምላኬ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ድንቢጦች ለመኖሪያቸው ጎጆ ሠርተዋል፤ ዋኖሶችም ጫጩቶቻቸውን የሚያኖሩበት በመሠዊያዎችህ አጠገብ ቤት አላቸው።
4
ዘወትር የምስጋና መዝሙር ለአንተ እያቀረቡ በመቅደስህ የሚኖሩ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
5
ወደ ጽዮን ተራራ መንፈሳዊ ጒዞ ለማድረግ የሚፈልጉና የአንተን ርዳታ የሚያገኙ እንዴት የተባረኩ ናቸው?
6
ባካ በተባለው ደረቅ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ እግዚአብሔር ምንጭን ያፈልቅላቸዋል፤ የበልግም ዝናብ ኩሬዎችን ይሞላቸዋል።
7
በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤ የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል።
8
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ! አድምጠኝ።
9
አምላክ ሆይ! መርጠህ የቀባኸውን ንጉሣችንን ባርከው፤ ጋሻችን ስለ ሆነም ተመልከተው።
10
በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤ በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ።
11
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
12
የሠራዊት አምላክ ሆይ! በአንተ የሚታመኑ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
← Chapter 83
Chapter 85 →