bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 63
Psalms 63
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።
2
በመቅደስህ ውስጥ አንተን ተመለከትኩ፤ ኀይልህንና ክብርህንም አየሁ።
3
ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ።
4
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ለጸሎትም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
5
ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ።
6
በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ።
7
አንተ ረዳት ስለ ሆንከኝ በጥበቃህ ሥር ተጠልዬ፥ በደስታ እዘምራለሁ።
8
ወደ አንተ እጠጋለሁ፤ ቀኝ እጅህም ቀና አድርጎ ይደግፈኛል።
9
እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ።
10
በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሬሳቸውንም ቀበሮዎች ይበሉታል።
11
እግዚአብሔር ድልን ስለሚያጐናጽፈው ንጉሡ ደስ ይለዋል፤ በእግዚአብሔር ስም የሚምሉ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሐሰተኞች አንደበት ግን ይዘጋል።
← Chapter 62
Chapter 64 →