bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 64
Psalms 64
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ! በችግሬ ምክንያት ወደ አንተ ስጸልይ ስማ፤ ከጠላት ማስፈራራትም ጠብቀኝ።
2
ከክፉዎች ምሥጢራዊ ሤራና ከክፉ አድራጊዎች ዕቅድ ጠብቀኝ።
3
እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤ እጅግ የከፋ ቃላትን እንደ ፍላጻ አነጣጥረው ይወረውራሉ።
4
እነርሱም ያለ ፍርሀት ንጹሑን ሰው ሸምቀው ይነድፉታል።
5
ክፉ ሤራ ለማቀነባበር እርስ በርሳቸው ይመካከራሉ፤ ወጥመዳቸውንም የት እንደሚዘረጉ ያቅዳሉ፤ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ “ማንም ሊያየን አይችልም” ይላሉ።
6
እነርሱ ክፉ ዕቅድ ዐቀዱ፤ “በሐሳባቸውም የተቀናጀ ወንጀል እንሠራለን” ይላሉ፤ ይህም የሰው ልብና የሰው አእምሮ በተንኰል የተሞላ መሆኑን ያሳያል።
7
እግዚአብሔር ግን ፍላጻዎችን ወደ እነርሱ ይወረውራል፤ እነርሱም በድንገት ይቈስላሉ።
8
እግዚአብሔር ንግግራቸው በራሳቸው ላይ ተመልሶ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል። የሚያዩአቸው ሁሉ በፍርሃት ከእነርሱ ይሸሻሉ።
9
ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤ ስለ እግዚአብሔር ሥራ ይናገራሉ፤ ስላደረገውም ነገር ያሰላስላሉ።
10
ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላቸው እርሱንም ከለላ ያድርጉ፤ ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ ያመስግኑት።
← Chapter 63
Chapter 65 →