bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 62
Psalms 62
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
2
ያለ እርሱ የሚጠብቀኝና የሚያድነኝ የለም፤ መከላከያዬም እርሱ ስለ ሆነ ከቶ አልናወጥም።
3
እንደ አረጀ ግድግዳና እንደ ተነቃነቀ አጥር ዐቅም ያነሰውን ሰው፥ ሁላችሁም በእርሱ ላይ አደጋ እየጣላችሁ። እስከ መቼ ስታጠቁት ትኖራላችሁ?
4
እነርሱ የሚፈልጉት ክብሩን ለመሻር ስለ ሆነ በእርሱ ላይ ሐሰት መናገርን ይወዳሉ፤ በአፋቸው ይመርቁታል፤ በልባቸው ግን ይረግሙታል።
5
እግዚአብሔርን ብቻ ጸጥ ብዬ እጠብቃለሁ፤ ተስፋዬም የሚመጣው ከእርሱ ነው።
6
የሚያድነኝ ኀያል አምባዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እርሱም እምነት የምጥልበት ምሽጌ ስለ ሆነ አልናወጥም።
7
መዳኔና ክብሬ የተገኘው ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ የመጠጊያዬ አምባና መጠለያዬ ነው።
8
ሕዝቦች ሆይ! ዘወትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ መጠጊያችን ስለ ሆነ የልባችሁን ሐሳብ ሁሉ ለእርሱ አቅርቡ።
9
ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።
10
በብዝበዛ አትመኩ፤ በቀማችሁትም ነገር ለመክበር ተስፋ አታድርጉ፤ ሀብታችሁ ቢበዛ እንኳ በእርሱ አትተማመኑ።
11
እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናግሮአል፤ ኀይል የእግዚአብሔር መሆኑን ሁለት ጊዜ ሰምቼአለሁ።
12
ጌታ ሆይ! ለሁሉም እንደየሥራው ስለምትከፍል ዘለዓለማዊ ፍቅር ያንተ ነው።
← Chapter 61
Chapter 63 →