bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 61
Psalms 61
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ! ጩኸቴን አድምጥ፤ ጸሎቴንም ስማ።
2
ተስፋ ቈርጬ ሳለ ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ከእኔ በላይ ወደ አለው ከፍተኛ አምባ ምራኝ።
3
አንተ ጠባቂዬና ከጠላቶቼ የምከለልብህ ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
4
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በቤትህ እንድኖርና በጥበቃህ ሥር መጠለያ እንዳገኝ ፍቀድልኝ።
5
አምላክ ሆይ! ስእለቴን ሰማህ፤ አንተን ለሚፈሩ ሰዎች ያዘጋጀኸውን በረከት ለእኔም ሰጠኸኝ።
6
በንጉሡ ዕድሜ ላይ ብዙ ዓመቶች ጨምርለት፤ ለብዙ ዘመንም እንዲኖር አድርገው!
7
አምላክ ሆይ! በፊትህ ለዘለዓለም እንዲነግሥ አድርገው፤ በዘለዓለማዊው ፍቅርህና በታማኝነትህ ጠብቀው።
8
ለአንተ የተሳልኩትን በየቀኑ በማቅረብ ዘወትር የምስጋና መዝሙር እዘምርልሃለሁ።
← Chapter 60
Chapter 62 →