bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 16
Psalms 16
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
አምላክ ሆይ! የምታመነው በአንተ ስለ ሆነ ጠብቀኝ፤
2
እግዚአብሔርን “አንተ ጌታዬ ነህ፤ ያለኝ መልካም ነገር ሁሉ ያንተ ስጦታ ነው” አልኩት።
3
በምድር ላይ የሚኖሩ ቅዱሳን የተከበሩ ናቸው፤ በእነርሱም እደሰታለሁ።
4
ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤ እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤ እነርሱንም አላመልክም።
5
እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ።
6
ለእኔ የተለኩልኝ የድንበር መስመሮች ያረፉት በሚያስደስቱ ቦታዎች ላይ ነው፤ በእርግጥ እኔ የሚያስደስት ርስት አለኝ።
7
የሚመክረኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሌሊት እንኳ ሕሊናዬ ያስተምረኛል።
8
ዘወትር እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱም በቀኜ ስለ ሆነ አልታወከም።
9
ስለዚህ ልቤ ተደስቶ ይፈነጥዛል፤ ሰውነቴም ያለ ስጋት ያርፋል።
10
ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ታማኝህንም መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም።
11
የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።
← Chapter 15
Chapter 17 →