bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 17
Psalms 17
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ።
2
ዐይኖችህ እውነትን ማየት ስለሚችሉ አንተ ብቻ ልትፈርድልኝ ትችላለህ።
3
ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥ ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም።
4
የሰዎችን ሥራ በሚመለከት፥ አንተ በተናገርከው ቃል መሠረት፥ እኔ ከዐመፀኞች አካሄድ ራሴን ጠብቄአለሁ።
5
ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።
6
አምላክ ሆይ! ልመናዬን ስለምትሰማ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።
7
የአንተን ከለላ ለሚፈልጉ፥ በቀኝ እጅህ የምታድናቸው አምላክ ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህን በአስደናቂ ሁኔታ ግለጥ።
8
የዐይን ብሌን በጥንቃቄ የሚጠበቀውን ያኽል ጠብቀኝ፤ በጥበቃህ ውስጥ ሰውረኝ።
9
ከበባ አድርገው ከሚያጠፉኝ ጨካኝ ጠላቶቼ ጠብቀኝ።
10
እነርሱ ለርኅራኄ ልባቸውን ዘግተዋል፤ አፋቸውም ትዕቢትን ይናገራል።
11
ጠላቶቼ አስጨነቁኝ፤ ከበባም አደረጉብኝ፤ ወደ መሬት ሊጥሉኝም ዐይናቸውን ጣሉብኝ።
12
እነርሱ እንደ ተራቡ አንበሶች ወይም እንደ ሸመቁ ደቦል አንበሶች ናቸው።
13
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥና ጣላቸው፤ በሰይፍህም ሕይወቴን ከክፉዎች አድን።
14
እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።
15
እኔ በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ በምነቃበት ጊዜም የአንተን አምሳያ በማየቴ እደሰታለሁ።
← Chapter 16
Chapter 18 →