bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 15
Psalms 15
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! ወደ መኖሪያህ መግባት የሚችል ማን ነው? በተቀደሰችው ተራራህስ ላይ ሊኖር የሚችል ማን ነው?
2
እርሱ ነቀፋ የሌለበት ሕይወትን የሚኖርና ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግ፥ ከልቡም እውነትን የሚናገር፥
3
ሌሎች ሰዎችን የማያማ፥ በጓደኞቹ ላይ ክፉ ነገር የማያደርግ፥ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታን የማያሠራጭ፥
4
ክፉ ሰዎችን የሚንቅ፥ ለእግዚአብሔር የሚታዘዙትን ግን የሚያከብር፥ ምንም ያኽል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል ኪዳን የሚፈጽም፥
5
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
← Chapter 14
Chapter 16 →