bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 12
Psalms 12
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ! አንድም ታማኝ ሰው ስላልቀረ እባክህ እርዳን፤ ታማኞች ሰዎች በሰው ዘር መካከል ጠፍተዋል።
2
አንዱ ለአንዱ ውሸትን ይናገራል፤ በሚያቈላምጥ አንደበት የሚናገሩትም በሁለት ልብ ነው።
3
እግዚአብሔር ሆይ! የሚያቈላምጡ ከንፈሮችንና የሚመኩ አንደበቶችን ዝጋ።
4
እነርሱ፦ “በመናገራችን የፈለግነውን እናገኛለን፤ እንደ ፈቀድን እንናገራለን፤ ሊከለክለን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።
5
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
6
የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው።
7
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ሁልጊዜ ጠብቀን፤ ክፉ ከሆኑት ከዚህ ዘመን ሰዎች አድነን።
8
ክፉ ነገር በሰዎች ዘንድ በሚመሰገንበት ጊዜ ክፉ ሰዎች በኩራት ይመላለሱበታል።
← Chapter 11
Chapter 13 →