bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 11
Psalms 11
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ከለላዬ ነው፤ እንዴት “እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ሽሽ” ትሉኛላችሁ።
2
ኃጢአተኞች በጨለማ አድብተው ልበቅኖችን ለመግደል ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋል።
3
መሠረቶች ሲፈርሱ ጻድቅ ሰው ምን ማድረግ ይችላል?
4
እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ነው፤ ዙፋኑም በሰማይ ነው፤ የሰውን ልጆች ይመለከታል። አተኲሮም በማየት ዐይኖቹም ይመረምሩአቸዋል።
5
እግዚአብሔር ጻድቃንንና ኃጢአተኞችን ይፈትናል፤ ዐመፅ የሚወዱትን ግን ይጠላቸዋል።
6
በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል፤ የሚጋረፍ ነፋስም የእነርሱ ዕድል ፈንታ ነው።
7
እግዚአብሔር ጻድቅ ስለ ሆነ የጽድቅን ሥራ ይወዳል፤ ትክክለኛ ሥራ የሚሠራ ሰው ሁሉ ፊቱን ያያል።
← Chapter 10
Chapter 12 →