bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 13
Psalms 13
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ሆይ፥ እስከ መቼ ትረሳኛለህ? የምትረሳኝ ለዘለዓለም ነውን? እስከ መቼስ ከእኔ ትሰወራለህ?
2
ችግርን እስከ መቼ መቻል ይኖርብኛል? እስከ መቼ ልቤ ቀንና ሌሊት በሐዘን ይሞላል? እስከ መቼስ ጠላቴ በእኔ ላይ የበላይነትን ያገኛል?
3
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እባክህ አድምጠኝና መልስ ስጠኝ፤ የሞት እንቅልፍ አንቀላፍቼ እንዳልወድቅ ብርታቱን ስጠኝ።
4
ጠላቶቼ “አሸነፍነው” ብለው እንዲመኩ፥ በእኔም መውደቅ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።
5
እኔ በማያቋርጥ ፍቅርህ እተማመናለሁ፤ በማዳንህ እደሰታለሁ።
6
እግዚአብሔር ሆይ! በጎ ነገር ስላደረግህልኝ ለአንተ እዘምራለሁ።
← Chapter 12
Chapter 14 →