bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 113
Psalms 113
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ይመስገን! እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ!
2
አሁንም ለዘለዓለም ስሙ ይመስገን።
3
ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!
4
እግዚአብሔር የመንግሥታት ሁሉ ገዢ ነው፤ ክብሩም ከሰማያት ሁሉ በላይ ነው።
5
እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም፤ ዙፋኑም ከሁሉ በላይ ነው።
6
ነገር ግን ሰማይንና ምድርን ወደ ታች ይመለከታል።
7
ድኾችን ከትቢያ ችግረኞችንም ከዐመድ ቊልል ያነሣቸዋል።
8
የልዑላን ጓደኞች ያደርጋቸዋል፤ ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያስቀምጣቸዋል።
9
መኻኒቱንም በቤቷ በክብር ያኖራታል፤ ልጆችንም በመስጠት ደስ ያሰኛታል። እግዚአብሔር ይመስገን!
← Chapter 112
Chapter 114 →