bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 114
Psalms 114
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
የያዕቆብ ዘሮች የሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ በመውጣት የባዕድን አገር በለቀቁ ጊዜ
2
ይሁዳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሆነ፤ እስራኤልም የእግዚአብሔር ርስት ሆነ።
3
ባሕር ይህን አይቶ ሸሸ፤ የዮርዳኖስም ወንዝ ውሃ ማፍሰሱን አቁሞ ወደ ኋላው ተመለሰ።
4
ተራራዎች እንደ አውራ በጎች ፈነጩ፤ ኰረብቶችም እንደ በግ ግልገል በየቦታው ዘለሉ።
5
አንተ ባሕር፥ ምን ሆነህ ሸሸህ? አንተስ ዮርዳኖስ፥ ስለምን መፍሰስህን አቁመህ ወደ ኋላህ ተመለስህ?
6
እናንተ ተራራዎች፥ ስለምን እንደ አውራ በጎች ፈነጫችሁ? እናንተስ ኰረብቶች፥ ስለምን እንደ በግ ግልገል በየቦታው ዘለላችሁ?
7
ምድር ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት፥ በያዕቆብም አምላክ ፊት በፍርሃት ተንቀጥቀጪ።
8
እርሱ አለቱን ወደ ኩሬ ውሃ፥ ጭንጫውንም ሸንተረር ወደ ወራጅ ምንጭ ይለውጣል።
← Chapter 113
Chapter 115 →