bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 112
Psalms 112
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ይመስገን! እግዚአብሔርን የሚፈራና ትእዛዞቹንም በመፈጸም እጅግ ደስ የሚለው ሰው እንዴት የተባረከ ነው!
2
የደግ ሰው ልጆች በምድር ላይ ብርቱዎች ይሆናሉ፤ የቅኖች ትውልድ ይባረካል።
3
ቤተሰቦቹ ሀብታሞችና ባለጸጎች ይሆናሉ፤ ጽድቅም ለዘለዓለም የእርሱ ይሆናል።
4
ምሕረትና ቸርነት፥ ቅንነትም ለሚያደርግ ለደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
5
ሥራውን በቅንነት የሚመራ፥ ለጋሥ የሆነና ሳይሰስት የሚያበድር ኑሮው የተሳካለት ይሆናል።
6
በእውነት እርሱ ምንጊዜም ቢሆን አይናወጥም፤ ጻድቅ ሰው ለዘለዓለም ይታሰባል።
7
እምነቱ ጽኑ ስለ ሆነና በእግዚአብሔርም ስለሚተማመን፥ ክፉ ወሬ አያስደነግጠውም።
8
በእግዚአብሔር ያለው እምነት እጅግ የጸና ስለ ሆነ ከቶ አይፈራም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
9
ለችግረኞች በልግሥና ይሰጣል፤ ቸርነቱም የማያቋርጥ ነው፤ ኀይልንና ክብርን ይጐናጸፋል።
10
ክፉዎች ይህን አይተው ይቈጣሉ፤ ተስፋ በመቊረጥም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ የክፉዎችም ምኞት ከንቱ ይሆናል።
← Chapter 111
Chapter 113 →