bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
/
Psalms 111
Psalms 111
Amharic New Standard Translation (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም) 2005
1
እግዚአብሔር ይመስገን! በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
2
እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርጎአል፤ በእርሱ አስደናቂ ሥራዎች የሚደሰት ሁሉ ያስባቸዋል።
3
የእግዚአብሔር ሥራ በክብርና በግርማ የተሞላ ነው፤ ጽድቁም ዘለዓለማዊ ነው።
4
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነው፤ በአስደናቂ ሥራውም የገነነ ነው።
5
ለሚፈሩት ሁሉ ምግባቸውን ያዘጋጅላቸዋል፤ ቃል ኪዳኑንም ከቶ አይረሳም።
6
የሕዝቦችን ርስት በመስጠት ታላቅ ኀይሉን ለወገኖቹ አሳይቶአል።
7
የሚያደርገው ሁሉ እውነትና ትክክል ነው፤ ትእዛዞቹም የታመኑ ናቸው።
8
እነርሱም ለዘለዓለም የጸኑ ናቸው፤ የተሰጡትም በእውነትና በታማኝነት ነው።
9
ለድኾች በልግሥና ይሰጣል፤ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳኑንም ሰጠ፤ ስሙም ቅዱስና አስፈሪ ነው።
10
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
← Chapter 110
Chapter 112 →