bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Song of Solomon 7
Song of Solomon 7
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አንቺ የልዑል ልጅ ሆይ፤ ነጠላ ጫማ የተጫሙ እግሮችሽ፣ እንዴት ያምራሉ! ሞገስን የተጐናጸፉ ዳሌዎችሽ፣ ብልኅ አንጥረኛ የተጠበባቸውን የዕንሐብል ይመስላሉ።
2
ዕንብርትሽ ጥሩ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት፣ እንደ ክብ ጽዋ ነው፤ ወገብሽ ዙሪያውን በውብ አበባ የታሰረ፣ የስንዴ ክምር ይመስላል።
3
ሁለት ጡቶችሽ፣ መንታ የዋሊያ ግልገሎችን ይመስላሉ።
4
ዐንገትሽ በዝኆን ጥርስ እንዳጌጠ መጠበቂያ ማማ ነው፤ ዐይኖችሽ በባትረቢ በር አጠገብ እንዳሉት፣ እንደ ሐሴቦን ኵሬዎች ናቸው፤ አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከት፣ እንደ ሊባኖስ መጠበቂያ ማማ ነው።
5
የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ አክሊል ሆኖልሻል፤ ጠጕርሽ የሐር ጕንጕን የመሰለ ነው፤ ንጉሡም በሹሩባሽ ታስሮ ተይዟል።
6
እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ የምትይ ነሽ! ፍቅሬ ሆይ፤ የምታስደስቺ ነሽ።
7
ቁመናሽ እንደ ዘንባባ ዛፍ መለል ያለ ነው፤ ጡቶችሽም የፍሬውን ዘለላ ይመስላሉ።
8
እኔም፣ “የዘንባባውን ዛፍ እወጣለሁ፤ ዘለላዎቹንም እይዛለሁ” አልሁ። ጡቶችሽ የወይን ዘለላ፣ የእስትንፋስሽም መዐዛ እንደ እንኮይ ፍሬ ይሁኑ፤
9
ከናፍሮችሽም እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ይጣፍጡ። የወይን ጠጁ በቀስታ እየተንቈረቈረ፣ ወደ ውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች ይውረድ።
10
እኔ የውዴ ነኝ፤ የእርሱም ምኞት እኔው ነኝ።
11
ውዴ ሆይ፤ ና ወደ ገጠር እንሂድ፤ ወደ መንደርም ገብተን እንደር፤
12
ማልደን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፣ ወይኑ እንቡጥ አውጥቶ፣ አበባው ፈክቶ፣ ሮማኑ አፍርቶ እንደ ሆነ እንይ፤ በዚያም ራሴን በፍቅር እሰጥሃለሁ።
13
ትርንጐዎች መዐዛቸውን ሰጡ፤ አዲስ የተቀጠፈውም ሆነ የበሰለው፣ ጣፋጩ ፍሬ ሁሉ በደጃፋችን አለ፤ ውዴ ሆይ፤ ለአንተ አስቀምጬልሃለሁ።
← Chapter 6
Chapter 8 →