bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Song of Solomon 6
Song of Solomon 6
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ወዴት ሄደ? አብረንሽም እንድንፈልገው፣ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው?
2
ውዴ መንጋውን ለማሰማራት፣ ውብ አበቦችንም ለመሰብሰብ፣ የቅመማ ቅመም መደቦቹ ወዳሉበት፣ ወደ አትክልት ቦታው ወርዷል።
3
እኔ የውዴ ነኝ፤ ውዴም የእኔ ነው፤ መንጋውንም በውብ አበቦች መካከል ያሰማራል።
4
ውዴ ሆይ፤ አንቺ እንደ ቴርሳ የተዋብሽ፣ እንደ ኢየሩሳሌም ያማርሽ፣ ዐርማቸውን እንደ ያዙ ወታደሮችም ግርማን የተጐናጸፍሽ ነሽ።
5
አስጨንቀውኛልና፣ እባክሽ ዐይኖችሽን ከእኔ ላይ አንሺ፤ ጠጕርሽ ከገለዓድ ተራራ የሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ይመስላል።
6
ጥርሶችሽ ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።
7
ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጕንጮችሽ፣ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።
8
ስድሳ ንግሥቶች፣ ሰማንያ ቁባቶች፣ ቍጥራቸውም የበዛ ደናግል ሊኖሩ ይችላሉ፤
9
እንከን የሌለባት ርግቤ ግን ልዩ ናት፤ እርሷ ለወለደቻት የተመረጠች፣ ለእናቷም አንዲት ናት፤ ቈነጃጅት አይተው “የተባረክሽ ነሽ” አሏት፤ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኗት።
10
እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣ እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?
11
በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀሉትን አትክልቶች ለማየት፣ ወይኑ ማቈጥቈጡን፣ ሮማኑ ማበቡን ለመመልከት፣ ወደ ለውዙ ተክል ቦታ ወረድሁ።
12
ይህን ከማወቄ በፊት፣ ምኞቴ በሕዝቤ ንጉሣዊ ሠረገሎች መካከል አስቀመጠኝ።
13
አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፤ ተመለሺ፤ ኧረ ተመለሺ፤ እንድናይሽ ተመለሺ፤ እባክሽ ተመለሺ። የመሃናይምን ዘፈን እንደሚመለከት ሰው፣ ሱላማጢስን የምትመለከቷት ለምንድን ነው?
← Chapter 5
Chapter 7 →