bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Song of Solomon 8
Song of Solomon 8
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ፣ እንደ ወንድሜ በሆንህ! ከዚያም ውጭ ባገኝህ፣ እስምህ ነበር፤ ታዲያ ማንም ባልናቀኝ!
2
እኔም ወደ አስተማረችኝ፣ ወደ እናቴም ቤት፣ እጅህን ይዤ በወሰድሁህ ነበር፤ የምትጠጣውን ጣፋጭ የወይን ጠጅ፣ የሮማኔን ጭማቂም በሰጠሁህ።
3
ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ ቀኝ እጁም ዐቅፎኛል።
4
እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት እማጠናችኋለሁ።
5
ውዷን ተደግፋ፣ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ ዛፍ ሥር አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤ በዚያም ታምጥ የነበረችው አንተን ወለደችህ።
6
በልብህ እንዳለ፣ በክንድህም እንደምትይዘው ማኅተም አስቀምጠኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣ ቅናቷም እንደ መቃብር ጨካኝ ናትና፤ እንደሚንቦገቦግ እሳት፣ እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነድዳለች።
7
የውሃ ብዛት ፍቅርን ሊያጠፋ አይችልም፤ ፈሳሾችም አያሰጥሟትም፤ ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይናቃል።
8
ትንሽ እኅት አለችን፤ ጡትም ገና አላወጣችም፤ ስለ እርሷ በምንጠየቅበት ቀን ምን ማድረግ እንችል ይሆን?
9
እርሷ ቅጥር ብትሆን፣ በላይዋ የብር መጠበቂያ ማማ እንሠራባታለን፤ በር ብትሆን፣ በዝግባ ዕንጨት እንከልላታለን።
10
እነሆ እኔ ቅጥር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ማማ ግንቦች ናቸው፤ እኔም በዐይኖቹ ፊት፣ ሰላምን እንደሚያመጣ ሰው ሆንሁ።
11
ሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑን ተክል ቦታም ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም የፍሬውን ዋጋ፣ አንድ አንድ ሺሕ ሰቅል ብር ያመጡለት ነበር።
12
የወይኔ ተክል ቦታ የራሴ፣ የግሌ ነው፤ ሰሎሞን ሆይ፤ አንድ ሺሁ ሰቅል ለአንተ፤ ፍሬውን ለሚጠብቁ ደግም ሁለት መቶ ይሁን።
13
አንቺ በአትክልቱ ቦታ የምትኖሪ ሆይ፤ ባልንጀሮቼ ድምፅሽን ይሰማሉ፤ እስቲ እኔም ልስማው።
14
ውዴ ሆይ፤ ቶሎ ናልኝ፤ ሚዳቋን፣ ወይም በቅመም ተራራ ላይ የሚዘልል፣ የዋሊያን ግልገል ምሰል።
← Chapter 7