bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 98
Psalms 98
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤ እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም ማዳንን አድርገውለታል።
2
እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።
3
ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ ታማኝነቱንም ዐሰበ፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን አዩ።
4
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
5
ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤ በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤
6
በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣ በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።
7
ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።
8
ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፣ ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤
9
እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤ እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።
← Chapter 97
Chapter 99 →