bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 97
Psalms 97
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ደስ ይበላት፤ በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ።
2
ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
3
እሳት በፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል።
4
መብረቁ ዓለምን አበራ፤ ምድርም አይታ ተንቀጠቀጠች።
5
ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት፣ በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።
6
ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ።
7
ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ፣ በጣዖታትም የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ፤ እናንተ አማልክት ሁሉ፤ ለእርሱ ስገዱ።
8
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ።
9
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል ነህና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ።
10
እግዚአብሔርን የምትወድዱ ክፋትን ጥሉ፤ እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል።
11
ብርሃን ለጻድቃን፣ ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።
12
እናንት ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።
← Chapter 96
Chapter 98 →