bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 99
Psalms 99
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ።
2
እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ብሏል።
3
ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ፤ እርሱ ቅዱስ ነው።
4
ፍትሕን የምትወድድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤ ፍትሕንና ቅንነትንም፣ ለያዕቆብ አደረግህ።
5
አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤ በእግሩ መርገጫ ስገዱ፤ እርሱ ቅዱስ ነውና።
6
ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤ እርሱም መለሰላቸው።
7
ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤ እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ።
8
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ አንተ መለስህላቸው፤ ጥፋታቸውን ብትበቀልም እንኳ፣ አንተ ይቅር የምትላቸው አምላክ ነህ።
9
አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤ በቅዱስ ተራራውም ላይ ስገዱ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።
← Chapter 98
Chapter 100 →