bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 9
Psalms 9
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ።
2
በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።
3
ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣ ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤
4
ፍርዴም ጕዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤ ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።
5
ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤ ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ።
6
ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤ ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤ መታሰቢያቸውም ተደምስሷል።
7
እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤ መንበሩንም ለፍርድ አጽንቷል።
8
ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።
9
እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።
10
ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።
11
በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤
12
ደም ተበቃዩ ዐስቧቸዋልና፤ የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም።
13
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤ አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤
14
ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣ ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤ በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።
15
አሕዛብ በቈፈሩት ጕድጓድ ገቡ፤ እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።
16
እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤ ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ።
17
ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።
18
ችግረኞች ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤ የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።
19
እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ ሰውም አያይል፤ አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።
20
እግዚአብሔር ሆይ፤ ድንጋጤ አምጣባቸው፤ ሕዝቦች ሰው ከመሆን እንደማያልፉ ይወቁ።
← Chapter 8
Chapter 10 →