bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 10
Psalms 10
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ?
2
ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።
3
ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።
4
ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤ በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤
5
መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው። በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል።
6
በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል።
7
አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ።
8
በየመንደሩ ሥርቻ ያደፍጣል፤ ንጹሓንን በሰዋራ ስፍራ ይገድላል። ዐይኖቹንም በምስኪኖች ላይ ያነጣጥራል።
9
በደኑ ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል፤ ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፤ ድኻውንም አፈፍ አድርጎ በወጥመዱ ይጐትታል።
10
ምስኪኑም ይደቅቃል፤ ዐንገቱን ይደፋል፤ ያልታደለውም በክንዱ ሥር ይወድቃል።
11
በልቡም፣ “እግዚአብሔር ረስቷል፤ ፊቱን ሸፍኗል፤ ፈጽሞም አያይም” ይላል።
12
እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ አምላክ ሆይ፤ ክንድህን አንሣ፤ ረዳት የሌላቸውንም አትርሳ።
13
ክፉ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ለምን ክፉ ይናገራል? በልቡስ፣ “ስለ ሥራዬ አይጠይቀኝም” ለምን ይላል?
14
አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
15
የክፉውንና የበደለኛውን ክንድ ስበር፤ የእጁንም ስጠው፤ ምንም እስከማይገኝ ድረስ።
16
እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው፤ ሕዝቦችም ከምድሩ ይጠፋሉ።
17
እግዚአብሔር ሆይ፤ የተገፉትን ምኞት ትሰማለህ፤ ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጆሮህንም ወደ እነርሱ ጣል ታደርጋለህ፤
18
ከዐፈር የተፈጠረ ሰው ከእንግዲህ እንዳያስጨንቃቸው፣ አንተ ለድኻ ዐደጉና ለተገፋው ትሟገታለህ።
← Chapter 9
Chapter 11 →