bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 8
Psalms 8
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው! ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ ከፍ ከፍ ብሏል።
2
ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ ምስጋናን አዘጋጀህ፤ ከጠላትህ የተነሣ፣ ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ።
3
የጣቶችህን ሥራ፣ ሰማያትህን ስመለከት፣ በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣
4
በዐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
5
ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ የክብርንና የሞገስን ዘውድ አቀዳጀኸው።
6
በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛህለት፤
7
በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣ የዱር አራዊትንም፣
8
የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሦችን፣ በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።
9
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!
← Chapter 7
Chapter 9 →