bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 83
Psalms 83
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤ አምላክ ሆይ፤ ጸጥ አትበል፤ ቸል አትበል።
2
ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።
3
በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤ በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።
4
“የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።
5
በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤ በአንተም ላይ ተማማሉ፤
6
የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣
7
ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር ሆነው ዶለቱ፤
8
አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፤ የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ።
9
በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤ በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።
10
እነርሱም በዐይንዶር ጠፉ፤ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ።
11
መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣ መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤
12
እነዚህም፣ “የእግዚአብሔርን የግጦሽ ቦታ፣ ወስደን የግላችን እናድርግ” የሚሉ ናቸው።
13
አምላኬ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዳ ትቢያ፣ በነፋስም ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው።
14
እሳት ደንን እንደሚያጋይ፣ ነበልባልም ተራራን እንደሚያቃጥል፣
15
እንዲሁ በሞገድህ አሳድዳቸው፤ በማዕበልህም አስደንግጣቸው።
16
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ ፊታቸውን በዕፍረት ሙላው፤
17
ለዘላለም ይፈሩ፤ ይታወኩም፤ በውርደትም ይጥፉ።
18
ስምህ እግዚአብሔር የሆነው አንተ ብቻ፣ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።
← Chapter 82
Chapter 84 →