bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 84
Psalms 84
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ ማደሪያህ ምንኛ የተወደደ ነው!
2
ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤ እጅግም ትጓጓለታለች፤ ልቤና ሥጋዬም፣ ለሕያው አምላክ እልል በሉ።
3
ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መሠዊያህ ባለበት ስፍራ፣ ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት፣ ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ጐጆ አገኘች።
4
በቤትህ የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል።
5
አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ ቡሩካን ናቸው።
6
በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣ የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤ የበልጕም ዝናብ ያረሰርሰዋል።
7
ከኀይል ወደ ኀይል ይሸጋገራሉ፤ እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል።
8
የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ አድምጠኝ።
9
አምላክ ሆይ፤ ጋሻችንን እይልን፤ የቀባኸውንም ተመልከት።
10
በሌላ ስፍራ ሺሕ ቀን ከመኖር፣ በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤ በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣ በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።
11
እግዚአብሔር አምላክ ፀሓይና ጋሻ ነውና፤ እግዚአብሔር ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን፣ መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።
12
የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ በአንተ የታመነ ሰው ቡሩክ ነው።
← Chapter 83
Chapter 85 →