bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 82
Psalms 82
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤ በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፤
2
“ፍትሕን የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው? ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው?
3
ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ ዐደጎች ፍረዱላቸው፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።
4
ወገን የሌለውንና ችግረኛውን ታደጉ፤ ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።
5
“ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤ በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6
“እኔም፤ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ’ አልሁ።
7
ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”
8
አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ በምድር ላይ ፍረድ፣ ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና።
← Chapter 81
Chapter 83 →