bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 81
Psalms 81
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ፤ ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ።
2
ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።
3
በሙሉ ጨረቃ፣ በክብረ በዓላችን ዕለት፣ በወሩ መግቢያ፣ ጨረቃ ስትወለድ መለከት ንፉ፤
4
ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ሥርዐት፣ የያዕቆብም አምላክ ድንጋጌ ነውና።
5
ሙሉ ለሙሉ ግብፅን ለቅቆ በወጣ ጊዜ፣ ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት፤ በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤
6
“ትከሻውን ከሸክም ገላገልሁት፤ እጁንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ።
7
በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግሁህ፤ በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ፤ በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ።
8
“ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤ እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ!
9
በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤ ለሌላም አምላክ አትስገድ።
10
ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ አፍህን በሰፊው ክፈተው፤ እኔም እሞላዋለሁ።
11
“ሕዝቤ ግን አላደመጠኝም፤ እስራኤልም እጅ አልሰጥ አለኝ።
12
ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣ አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።
13
“ምነው ሕዝቤ ቢያደምጠኝ ኖሮ፣ እስራኤል በመንገዴ በሄደ ኖሮ፣
14
ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባንበረከክኋቸው ነበር፤ እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር።
15
እግዚአብሔርን የሚጠሉ በፊቱ ይርዳሉ፤ ቅጣታቸውም እስከ ዘላለም የሚዘልቅ ነው።
16
እናንተን ግን ምርጡን ስንዴ አበላችኋለሁ፤ ከዐለቱም ማር አጠግባችኋለሁ።”
← Chapter 80
Chapter 82 →