bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 76
Psalms 76
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፤ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።
2
ድንኳኑ በሳሌም፣ ማደሪያውም በጽዮን ነው።
3
በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ።
4
አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል።
5
ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤ አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ ከጦረኞቹም መካከል፣ እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።
6
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ ፈረስና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል።
7
መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል?
8
አንተ ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፤ ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች፤
9
አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው።
10
ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ።
11
ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተሳሉ፤ ስእለቱንም አግቡ፤ በእርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ፣ አስፈሪ ለሆነው ለእርሱ እጅ መንሻ ያምጡ።
12
እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል፤ በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ነው።
← Chapter 75
Chapter 77 →