bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 75
Psalms 75
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ስምህ ቅርብ ነውና ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ሰዎችም ስለ ድንቅ ሥራህ ይናገራሉ።
2
አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣ በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ።
3
ምድርና ሕዝቦቿ ሁሉ በሚናወጡበት ጊዜ፣ ምሰሶዎቿን አጽንቼ የምይዝ እኔ ነኝ።
4
እብሪተኛውን፣ ‘አትደንፋ’፤ ክፉውንም ‘ቀንድህን ከፍ አታድርግ እለዋለሁ፤
5
ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር።’ ”
6
ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣምና፤
7
ነገር ግን የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ ያደርጋል።
8
በእግዚአብሔር እጅ ጽዋ አለ፤ በሚገባ የተቀመመና ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ ሞልቶበታል፤ ይህን ከውስጡ ወደ ውጭ ገለበጠው፤ የምድር ዐመፀኞችም አተላውን ሳይቀር ይጨልጡታል።
9
እኔ ግን ይህን ለዘላለም ዐውጃለሁ፤ ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬ አቀርባለሁ።
10
የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤ የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ ይላል።
← Chapter 74
Chapter 76 →