bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 77
Psalms 77
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ።
2
በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ ነፍሴም አልጽናና አለች።
3
አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች።
4
ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤ መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።
5
የድሮውን ዘመን አሰብሁ፤ የጥንቶቹን ዓመታት አውጠነጠንሁ።
6
ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ ከልቤም ጋር ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦
7
“ለመሆኑ፣ ጌታ ለዘላለም ይጥላልን? ከእንግዲህስ ከቶ በጎነትን አያሳይምን?
8
ምሕረቱስ ለዘላለም ጠፋን? የገባውስ ቃል እስከ ወዲያኛው ተሻረን?
9
እግዚአብሔር ቸርነቱን ዘነጋ? ወይስ ከቍጣው የተነሣ ርኅራኄውን ነፈገ?”
10
እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።
11
የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤ የጥንት ታምራትህን በርግጥ አስታውሳለሁ፤
12
ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ።
13
አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?
14
ታምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ በሕዝቦችም መካከል ኀይልህን ትገልጣለህ።
15
የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፣ ሕዝብህን በክንድህ ተቤዠሃቸው።
16
አምላክ ሆይ፤ ውሆች አዩህ፤ ውሆች አንተን አይተው ተሸማቀቁ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ።
17
ደመናት ውሃን አንጠባጠቡ፤ ሰማያት አንጐደጐዱ፤ ፍላጾችህም ዙሪያውን አብለጨለጩ።
18
የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ተሰማ፤ መብረቅህ ዓለምን አበራው፤ ምድርም ራደች፤ ተንቀጠቀጠች።
19
መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፤ መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።
20
በሙሴና በአሮን እጅ፣ ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው።
← Chapter 76
Chapter 78 →