bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 74
Psalms 74
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድን ነው? በማሰማሪያህ ባሉ በጎችህስ ላይ ቍጣህ ለምን ነደደ?
2
ጥንት ገንዘብህ ያደረግሃትን ጉባኤ፣ የዋጀሃትን የርስትህን ነገድ፣ መኖሪያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራ ዐስብ።
3
ርምጃህን ለዘላለሙ ባድማ ወደ ሆነው አቅና፤ ጠላት በመቅደስህ ውስጥ ያለውን ሁሉ አበላሽቷል።
4
ጠላቶችህ በመገናኛ ስፍራህ መካከል ደነፉ፤ አርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ።
5
በጫካ መካከል ዛፎችን ለመቍረጥ፣ መጥረቢያ የሚያነሣ ሰው መሰሉ።
6
በእደ ጥበብ ያጌጠውን ሥራ ሁሉ፣ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰባበሩት።
7
መቅደስህን አቃጥለው አወደሙት፤ የስምህንም ማደሪያ አረከሱ።
8
በልባቸውም፣ “ፈጽሞ እንጨቍናቸዋለን” አሉ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ የተመለከበትን ስፍራ ሁሉ አቃጠሉ።
9
የምናየው ምልክት የለም፤ ከእንግዲህ የሚነሣ አንድም ነቢይ የለም፤ ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል የሚያውቅ በእኛ ዘንድ የለም።
10
አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚያሾፈው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?
11
እጅህን ለምን ትሰበስባለህ? ቀኝ እጅህን ለምን በብብትህ ሥር ታቈያለህ?
12
አምላክ ሆይ፤ አንተ ከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነህ፤ በምድር ላይ ማዳንን አደረግህ።
13
ባሕርን በኀይልህ የከፈልህ አንተ ነህ፤ የባሕሩንም አውሬ ራሶች በውሃ ውስጥ ቀጠቀጥህ።
14
የሌዋታንን ራሶች አደቀቅህ፤ ለምድረ በዳ ፍጥረታትም ምግብ አድርገህ የሰጠሃቸው፣
15
ምንጮችንና ፈሳሾችን ያፈለቅህ አንተ ነህ፤ ሳያቋርጡ የሚፈስሱትንም ወንዞች አደረቅህ።
16
ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ ጨረቃንና ፀሓይን አንተ አጸናሃቸው።
17
የምድርን ዳርቻ ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ፤ በጋውንም ክረምቱንም አንተ ሠራህ።
18
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣ ከንቱ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ ዐስብ።
19
የርግብህን ነፍስ አሳልፈህ ለዱር አራዊት አትስጥ፤ የችግረኞች ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለሙ አትርሳ።
20
ኪዳንህን ዐስብ፤ የዐመፅ መናኸሪያ በምድሪቱ ጨለማ ስፍራዎች ሞልተዋልና።
21
የተጨቈኑት ዐፍረው አይመለሱ፤ ድኾችና ችግረኞች ስምህን ያመስግኑ።
22
አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለዐላማህ ተሟገት፤ ከንቱ ሰው ቀኑን ሙሉ እንደሚያላግጥብህ ዐስብ።
23
የባላጋራዎችህን ድንፋታ፣ ዘወትር የሚነሣውን የጠላቶችህን ፉከራ አትርሳ።
← Chapter 73
Chapter 75 →