bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 73
Psalms 73
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ልባቸው ንጹሕ ለሆነ፣ ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው!
2
እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ።
3
ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4
አንዳች ጣር የለባቸውም፤ ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው።
5
በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤ እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።
6
ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል።
7
የሠባ ዐይናቸው ይጕረጠረጣል፤ ልባቸውም በከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይፈስሳል።
8
በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ።
9
አፋቸውን በሰማይ ላይ ያላቅቃሉ፤ አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል።
10
ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይነጕዳል፤ ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ።
11
“ለመሆኑ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?” ይላሉ።
12
እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ ሁልጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።
13
ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል!
14
ቀኑን ሙሉ ተቀሠፍሁ፤ ጧት ጧትም ተቀጣሁ።
15
“እኔ እንደዚህ እናገራለሁ” ብልማ ኖሮ፣ የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር።
16
ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣ አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ።
17
ይኸውም ወደ አምላክ መቅደስ እስክገባ፣ መጨረሻቸውንም እስካይ ድረስ ነበር።
18
በርግጥ በሚያዳልጥ ስፍራ አስቀመጥሃቸው፤ ወደ ጥፋትም አወረድሃቸው።
19
እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ! በድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ።
20
ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፤ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እንደ ቅዠት ከንቱ ታደርጋቸዋለህ።
21
ነፍሴ በተማረረች ጊዜ፣ ልቤም በተቀሠፈ ጊዜ፣
22
ስሜት የሌለውና አላዋቂ ሆንሁ፤ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23
ይህም ሆኖ ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፤ አንተም ቀኝ እጄን ይዘኸኛል።
24
በምክርህ መራኸኝ፤ ኋላም ወደ ክብር ታስገባኛለህ።
25
በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምሻው የለኝም።
26
ሥጋዬና ልቤ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን የልቤ ብርታት፣ የዘላለም ዕድል ፈንታዬ ነው።
27
እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ አንተ ታማኞች ያልሆኑልህን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ።
28
ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ።
← Chapter 72
Chapter 74 →