bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 70
Psalms 70
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
2
ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ፣ ይፈሩ፤ ሁከትም ይምጣባቸው፤ የእኔን መጐዳት የሚመኙ፣ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
3
በእኔ ላይ፣ “ዕሠይ! ዕሠይ!” የሚሉ፣ ተሸማቅቀው ወደ ኋላ ይመለሱ።
4
ነገር ግን የሚሹህ ሁሉ፣ በአንተ ሐሤት ያድርጉ፤ ደስም ይበላቸው፤ “ማዳንህን የሚወድዱ ሁሉ ሁልጊዜ፣ እግዚአብሔር ከፍ ይበል!” ይበሉ።
5
እኔ ግን ምስኪንና ችግረኛ ነኝ፤ አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ ረዳቴም፣ ታዳጊዬም አንተ ነህና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።
← Chapter 69
Chapter 71 →