bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 71
Psalms 71
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ ከቶም አልፈር።
2
በጽድቅህ ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።
3
ምንጊዜም የምሸሽበት፣ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣ ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ።
4
አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።
5
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፣ ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።
6
ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤ አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።
7
ብዙዎች እንደ ጕድ አዩኝ፤ አንተ ግን ጽኑ ዐምባዬ ነህ።
8
ቀኑን ሙሉ ክብርህን ያወራ ዘንድ፣ አፌ በምስጋናህ ተሞልቷል።
9
በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ጕልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ።
10
ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና፣ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ በአንድ ላይ አሢረዋል፤
11
እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ትቶታል፤ የሚያስጥለው የለምና፣ ተከታትላችሁ ያዙት” አሉ።
12
አምላክ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ አምላኬ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
13
ባላንጣ የሆኑብኝ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ፣ ንቀትንና ውርደትን ይከናነቡ።
14
እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።
15
አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ ቀኑን ሙሉ ስለ ማዳንህ ይናገራል፤ ማቆሚያ ልኩንም አላውቅም።
16
መጥቼ የጌታ እግዚአብሔርን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ፤ የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።
17
አምላክ ሆይ፤ አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤ እኔም እስከ ዛሬ ድረስ ድንቅ ሥራህን ዐውጃለሁ።
18
አምላክ ሆይ፤ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ፤ ክንድህን ለመጭው ትውልድ፣ ኀይልህን ኋላ ለሚነሣ ሕዝብ ሁሉ፣ እስከምገልጽ ድረስ።
19
አምላክ ሆይ፤ ጽድቅህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ አንተ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፤ አምላክ ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
20
ብዙ መከራና ጭንቅ ብታሳየኝም፣ ሕይወቴን እንደ ገና ታድሳለህ፤ ከምድር ጥልቅም፣ እንደ ገና ታወጣኛለህ።
21
ክብሬን ትጨምራለህ፤ ተመልሰህም ታጽናናኛለህ።
22
አምላኬ ሆይ፤ ስለ ታማኝነትህ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፤ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።
23
ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤ አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።
24
አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ ቀኑን ሙሉ ያወራል፤ የእኔን መጐዳት የሚፈልጉ፣ ዐፍረዋልና፤ ተዋርደዋልም።
← Chapter 70
Chapter 72 →