bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 53
Psalms 53
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ቂል በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤ በጎ ነገርን የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም።
2
በማስተዋል የሚመላለስ፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3
ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤ በአንድነትም ተበላሹ፤ አንድ እንኳ በጎ የሚያደርግ የለም።
4
ሰው እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉት፣ እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት፣ እነዚያ ክፉ አድራጊዎች ከቶ አይማሩምን?
5
የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ፣ በፍርሀት ተዋጡ፤ እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤ እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው።
6
ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣ ያዕቆብ ሐሤት ያድርግ፤ እስራኤል ደስ ይበለው።
← Chapter 52
Chapter 54 →