bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 52
Psalms 52
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ? አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣ እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?
2
አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤ አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣ ጥፋትን ያውጠነጥናል።
3
ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣ እውነትን ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ወደድህ።
4
አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፤ ጐጂ ቃላትን ሁሉ ወደድህ!
5
እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ያንኰታኵትሃል፤ ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል።
6
ጻድቃን ይህን አይተው ይፈራሉ፤ እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
7
“እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣ ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ፣ በክፋቱም የበረታ፣ ያ ሰው እነሆ!”
8
እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት፣ እንደ ለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።
9
ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ ስምህ መልካም ነውና፣ ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።
← Chapter 51
Chapter 53 →