bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 54
Psalms 54
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ አድነኝ፤ በኀይልህም ፍረድልኝ።
2
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤ የአፌንም ቃል አድምጥ።
3
ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤ ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤ እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም።
4
እነሆ፤ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፤ ጌታም ደግፎ ይይዘኛል።
5
የገዛ ክፋታቸው በሚያደቡብኝ ላይ ይመለስባቸው፤ በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው።
6
በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ነውና፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤
7
ከመከራ ሁሉ ታድጎኛልና፤ ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቷል።
← Chapter 53
Chapter 55 →