bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 128
Psalms 128
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣ በመንገዱም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው።
2
የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤ ትባረካለህ፤ ይሳካልሃልም።
3
ሚስትህ በቤትህ፣ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣ እንደ ወይራ ተክል ናቸው።
4
እነሆ፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው፣ እንዲህ ይባረካል።
5
እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤
6
የልጅ ልጅ ለማየትም ያብቃህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።
← Chapter 127
Chapter 129 →