bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 127
Psalms 127
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2
የዕለት ጕርስ ለማግኘት በመጣር፣ ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤ እርሱ ለሚወድዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።
3
እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።
4
በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣ በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።
5
ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣ የተባረከ ሰው ነው፤ ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።
← Chapter 126
Chapter 128 →