bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 129
Psalms 129
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤
2
በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም።
3
ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ ትልማቸውንም አስረዘሙት።”
4
እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤ የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው።
5
ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
6
ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤
7
ደግሞም ለዐጫጅ እጁን፣ ለነዶ ሰብሳቢ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
8
መንገድ ዐላፊዎችም፣ “ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ።
← Chapter 128
Chapter 130 →