bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 126
Psalms 126
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።
2
በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
3
እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን።
4
እግዚአብሔር ሆይ፤ በኔጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣ ምርኳችንን መልስ።
5
በእንባ የሚዘሩ፣ በእልልታ ያጭዳሉ።
6
ዘር ቋጥረው፣ እያለቀሱ የተሰማሩ፣ ነዷቸውን ተሸክመው፣ እልል እያሉ ይመለሳሉ።
← Chapter 125
Chapter 127 →