bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 113
Psalms 113
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤ የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።
2
ከአሁን እስከ ዘላለም፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
3
ከፀሓይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ፣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
4
እግዚአብሔር ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5
እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ፣ በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?
6
በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣ ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?
7
ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤
8
ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤ ከሕዝቡም ሹማምት ጋር ያስቀምጠዋል።
9
መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል። ሃሌ ሉያ።
← Chapter 112
Chapter 114 →