bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 114
Psalms 114
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ሲሄድ፣ የያዕቆብም ቤት ቋንቋው ልዩ ከሆነ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ፣
2
ይሁዳ የእግዚአብሔር መቅደስ፣ እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።
3
ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
4
ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ።
5
አንቺ ባሕር፤ የሸሸሽው አንቺም ዮርዳኖስ ያፈገፈግሽው ለምንድን ነው?
6
እናንተ ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ለምን ዘለላችሁ?
7
ምድር ሆይ፤ በጌታ ፊት፣ በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፤
8
እርሱ ዐለቱን ወደ ኵሬ፣ ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ።
← Chapter 113
Chapter 115 →