bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 112
Psalms 112
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ በትእዛዙም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው።
2
ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3
ሀብትና ብልጽግና በቤቱ ይሞላል፤ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
4
ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
5
ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል፤
6
ለዘላለም ከስፍራው አይናወጥምና፤ ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል።
7
ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።
8
ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
9
በልግስና ለድኾች ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10
ክፉ ሰው ይህን በማየት ይበሳጫል፤ ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፤ የክፉዎችም ምኞት ትጠፋለች።
← Chapter 111
Chapter 113 →