bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 111
Psalms 111
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሃሌ ሉያ። በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
2
የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።
3
ሥራው ባለ ክብርና ባለ ግርማ ነው፤ ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
4
ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።
5
ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።
6
ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣ የአሠራሩን ብርታት አሳይቷል።
7
የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤ ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤
8
ከዘላለም እስከ ለዘላለም የጸና ነው፤ በእውነትና በቅንነትም የተሠራ ነው።
9
ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤ ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤ ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው።
10
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።
← Chapter 110
Chapter 112 →