bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 30
Job 30
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፣ ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጋር እንዳይቀመጡ፣ አባቶቻቸውን የናቅኋቸው፣ እነዚህ ይሣለቁብኛል።
2
ጕልበት የከዳቸው፣ የክንዳቸው ብርታት ምን ፋይዳ ይሞላልኝ ነበር?
3
ከችጋርና ከራብ የተነሣ ጠወለጉ፤ ሰው በማይኖርበት በረሓ፣ በደረቅም ምድር በሌሊት ተንከራተቱ።
4
ከቍጥቋጦ ምድር ጨው ጨው የሚል አትክልት ለቀሙ፤ ምግባቸውም የክትክታ ሥር ነበር።
5
ከኅብረተ ሰቡ ተለይተው ተባረሩ፤ ሰዎች እንደ ሌባ ይጮኹባቸዋል።
6
በዐለት መካከል በምድር ጕድጓድ፣ በደረቅ ሸለቆ ዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዱ።
7
በጫካ ውስጥ ያናፋሉ፤ በእሾኻማ ቍጥቋጦ መካከልም ይታፈጋሉ።
8
ስማቸው የማይታወቅ አልባሌ ናቸው፤ ከምድሪቱም ተባርረዋል።
9
“አሁን ግን ልጆቻቸው በዘፈን ይሣለቁብኛል፤ በእነርሱም ዘንድ መተረቻ ሆኛለሁ።
10
ይጸየፉኛል፣ ወደ እኔም አይቀርቡም፤ ያለ ምንም ይሉኝታ በፊቴ ይተፋሉ።
11
እግዚአብሔር የቀስቴን አውታር ስላላላውና በመከራም ስለ መታኝ፣ በፊቴ መቈጠብን ትተዋል።
12
በቀኜ በኩል ባለጌዎች ሆ! ብለው ተነሡብኝ፤ ለእግሬም ወጥመድ ዘረጉ፤ የዐፈር ድልድልም አዘጋጁብኝ።
13
መንገድ ዘጉብኝ፤ የሚገታቸው ሳይኖር፣ ሊያጠፉኝ ተነሡ።
14
በሰፊ ንቃቃት ውስጥ እንደሚመጣ ሰው መጡብኝ፤ በፍርስራሽም መካከል እየተንከባለሉ ደረሱብኝ።
15
በድንጋጤ ተውጫለሁ፤ ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዷል፤ በሰላም መኖሬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቷል።
16
“አሁን ነፍሴ በውስጤ ዐለቀች፤ የመከራ ዘመንም ይዞኛል።
17
ደዌ በሌሊት ዐጥንቴን ይበሳል፤ የሚቈረጥመኝም ፋታ አይሰጠኝም።
18
እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ልብሴን ጨምድዷል፤ በልብሴም ክሳድ ዐንቆ ይዞኛል።
19
እርሱ ጭቃ ውስጥ ጥሎኛል፤ እኔም ከዐፈርና ከዐመድ አልተሻልሁም።
20
“እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤ በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ።
21
ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤ በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ።
22
ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤ በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ።
23
ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።
24
“የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣ በርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም።
25
በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን? ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን?
26
ነገር ግን መልካም ስጠብቅ፣ ክፉ ነገር ደረሰብኝ፤ ብርሃንንም ስጠባበቅ፣ ጨለማ መጣብኝ።
27
በውስጤ ያለው ነውጥ አላቋረጠም፤ የመከራ ዘመንም መጣብኝ።
28
በፀሓይ አይደለም እንጂ፣ ጠቋቍሬ እዞራለሁ፤ በጉባኤ መካከል ቆሜ ለርዳታ እጮኻለሁ።
29
የቀበሮች ወንድም፣ የጕጕቶችም ባልንጀራ ሆኛለሁ።
30
ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ።
31
በገናዬ ለሐዘን፣ እንቢልታዬም ለልቅሶ ተቃኝቷል።
← Chapter 29
Chapter 31 →