bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 31
Job 31
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
“ወደ ኰረዳዪቱ ላለመመልከት፣ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።
2
ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሰው ዕድል ፈንታው፣ ከአርያም ሁሉን ከሚችል አምላክስ ዘንድ ቅርሱ ምንድን ነው?
3
ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን?
4
እርሱ መንገዴን አያይምን? ርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?
5
“በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ፣ እግሬም ወደ ሽንገላ ቸኵሎ ከሆነ፣
6
እግዚአብሔር በእውነተኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ።
7
አረማመዴ ከመንገድ ወጣ ብሎ፣ ልቤ ዐይኔን ተከትሎ፣ ወይም እጄ ረክሶ ከሆነ፣
8
የዘራሁትን ሌላ ይብላው፤ ሰብሌም ተነቅሎ ይጥፋ።
9
“ልቤ ሌላዋን ሴት ከጅሎ፣ በባልንጀራዬ ደጅ አድብቼ ከሆነ፣
10
ሚስቴ የሌላ ሰው እህል ትፍጭ፤ ሌሎች ሰዎችም ይተኟት፤
11
ይህ አሳፋሪ፣ ፍርድም የሚገባው ኀጢአት ነውና።
12
ይህ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ እሳት ነው፤ ቡቃያዬንም ባወደመ ነበር።
13
“ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቼ አቤቱታ ባቀረቡ ጊዜ፣ ፍርድ አዛብቼ ከሆነ፣
14
እግዚአብሔር ሲነሣ ምን አደርጋለሁ? ሲጠይቀኝስ ምን መልስ እሰጣለሁ?
15
እኔን በማሕፀን ውስጥ የፈጠረኝ እነርሱን የፈጠረ አይደለምን? በሆድ ውስጥ የሠራንስ እርሱ ራሱ አይደለምን?
16
“ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣
17
እንጀራዬን ከድኻ ዐደጉ ጋር ሳልካፈል፣ ለብቻዬ በልቼ ከሆነ፣
18
ይልቁን ድኻ ዐደጉን ከታናሽነቴ ጀምሮ እንደ አባት አሳደግሁት፤ መበለቲቱንም ከተወለድሁ ጀምሮ መንገድ መራኋት፤
19
በልብስ ዕጦት ሰው ሲጠፋ፣ ወይም ዕርቃኑን ያልሸፈነ ድኻ አይቼ፣
20
በበጎቼ ጠጕር ስላሞቅሁት፣ ልቡ ባርኮኝ ካልሆነ፣
21
በአደባባይ ተሰሚነት አለኝ ብዬ፣ በድኻ ዐደጉ ላይ እጄን አንሥቼ ከሆነ፣
22
ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይነቀል፤ ክንዴም ከመታጠፊያው ይሰበር፤
23
የእግዚአብሔርን ቍጣ በመፍራቴ፣ እንዲህ ያሉ ነገሮች መፈጸም አልቻልሁም።
24
“ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣
25
እጄ ባገኘችው ሀብት፣ በባለጠግነቴም ብዛት ደስ ብሎኝ ከሆነ፣
26
የፀሓይን ድምቀት አይቼ፣ ወይም የጨረቃን አካሄድ ግርማ ተመልክቼ፣
27
ልቤ በስውር ተታልሎ፣ ስለ ክብራቸው አፌ እጄን ስሞ ከሆነ፣
28
ለልዑል እግዚአብሔር ታማኝ አለመሆኔ ነውና፣ ይህም ደግሞ የሚያስቀጣኝ በደል በሆነ ነበር።
29
“በጠላቴ ውድቀት ደስ ብሎኝ፣ በደረሰበትም መከራ ሐሤት አድርጌ እንደ ሆነ፣
30
እኔ ግን በነፍሱ ላይ ክፉ እንዲመጣ በመራገም፣ አንደበቴን ለኀጢአት ከቶ አሳልፌ አልሰጠሁም።
31
የቤቴ ሰዎች፣ ‘ከኢዮብ ከብት ሥጋ አስቈርጦ፣ ያልጠገበ ማን ነው?’ ብለው ካልሆነ፣
32
ነገር ግን ቤቴ ለመንገደኛው ዘወትር ክፍት ስለ ነበር፣ መጻተኛው በጐዳና ላይ አያድርም ነበር።
33
ሰዎች እንደሚያደርጉት በደሌን በልቤ በመሰወር፣ ኀጢአቴን ሸሽጌ ከሆነ፣
34
ሕዝቡን በመፍራት፣ የወገኖቼንም ንቀት በመሸሽ፣ ወደ ደጅ ሳልወጣ፣ ዝም ብዬ ቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም።
35
“ምነው የሚሰማኝ ባገኝ! የመከላከያ ፊርማዬ እነሆ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፤ ከሳሼም ክሱን በጽሑፍ ያቅርብ።
36
በርግጥ ትከሻዬ ላይ በደረብሁት፣ እንደ አክሊልም ራሴ ላይ በደፋሁት ነበር።
37
እያንዳንዱን ርምጃዬን በገለጽሁለት፣ እንደ ልዑል እየተንጐራደድሁ በቀረብሁት ነበር።
38
“ዕርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ ከሆነ፣ ትልሞቿ ሁሉ በእንባ ርሰው እንደ ሆነ፣
39
ፍሬዋን ያለ ዋጋ በልቼ፣ የባለመሬቶቿን ነፍስ አሳዝኜ ከሆነ፣
40
በስንዴ ፈንታ እሾኽ፣ በገብስም ምትክ ዐረም ይብቀልብኝ።” የኢዮብ ቃል ተፈጸመ።
← Chapter 30
Chapter 32 →